www.guragezone.gov.et

አስተዳደር

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ራዕይ፤ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ (VISION)

ዞኑ የልማት፤የሠላምና የዲሞክራሲ ግንባታ ተፋጥኖ መልካም አስተዳደርና ብልጽግና ሰፍኖ ማየት

ተልዕኮ (MISSION)

የዞኑን ፤ተፈጥሮአዊና ሰብዓዊ ሀብቶች በአግባቡ በተቀናጀ መልኩ በጥቅም ላይ እንዲውሉ በማስተባበርና በመምራት ፤

የዞኑ ህብረተሰብ በልማትና በልማትና በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የተሟላ ተሳትፎ ኖሮት ተጠቃሚነቱን በማረጋገጥና ፤

ፍትህና ፤ሠላምና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ብልጽግና እንዲመጣ ማድረግ

እሴቶች (VALUES)

አለማዳላት

ለባህሎች ከበሬታ መስጠት

ቅን አገልጋይ መሆን

ተነሳሽነትን

ሙያዊ ብቃት

ግልጸኝነት

ሚስጥር መጠበቅ

ተሳትፎአዊነት

ጸረ- ሙሰኝነት

ቁጠባን ባህል ማድረግ

 

 

2.1.3. የሥራ ሂደቱ ተልዕኮ ፣ ራዕይ እና እሴቶች

ተልዕኮ

መመቴክን በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻልና መመቴክ ለዞናችን እድገት የሚሰጠውን ድጋፍ ማሳደግ፡፡

ራዕይ

በ 2012 ዓ.ም የሁሉም የዞናችን ህብረተሰብ ኑሮና ህይወት በመመቴክ የደገፈ ሆኖ ማየት

እሴቶች

 

ባለፉት ዓመታት በዞናችን የሰላም፣የዲሞክራሲና የልማት ተግባሮች ለማከናወን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተነደፈው በብቃት ሊያስፈጸም የሚችል አቅም የተሟላ ሊሆን ባለመቻሉ ከዞን እስከ ቀበሌ በአጠቃላይ የመንግስት መዋቅር የሚታየውን የማስፈጸም አቅም ችግሮችን ለመቅረፍ የአቅም ግንባታ ስትራቴጂዎችንና ፕሮግራሞችን የሚያስተባብርና በበላይነት የሚያስፈጽም ተቋማዊ አካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የክልሉን አስፈጻሚና ፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 36/1994 እንደገናም ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/95 የአቅም ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሆኖ ሲቋቋም የኢንፎርሚሸን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከ15 የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች እንደ አንድ አቅም ግንባታ ፕሮግራም ተቀርጾ ሲተገበር ቆይቷል፡፡ፕሮግራሙ 1996 ጀምሮ በቡድን ደረጃ እንዲሁም ከ 2000 ሃምሌ ጀምሮ በስራ ሂደት ሲሰራበት ቆይቷል፡፡ በመቀጠልም በክልሉ የአስፈጻሚ መ/ቤቶችን ለማደራጀትና ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 133/2002 መሰረት የመገናኛና መረጃ ቴክኖሎጂ የሥራ ሂደት ሆኖ በአስተዳደር መዋቅር ውስጥ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት /ከ1998-2002/ የስራ ክፍሉ በአቅም ግንባታ ሴክተር የተቀመጡ ግቦችና ስትራቴጂዎች ሲተገብር ቆይቷል፡፡ በተለይም የመንግስት መሥሪያ ቤቶችን አሰራር ቀልጣፋና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የደገፈ እንዲሆን ማድረግ አንዱ ነበር፡፡ በዚህም ረገድ በዋናነት ትኩረት ተሰጥቶት የተሰራው በዞኑ በየእርከኑ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት የመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ስልጠና ፣ ልዩ ልዩ የኔትወርክ ዝርጋታዎች ፣ የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገና ፣ ከክልሉ የመጡ አዳዲስ የኢኮቴ መሳሪያዎችን ማሰራጫት፣ የተዘረጋውን የትምህርት ቤትና የወረዳ ኔት መረብን በመከታተልና በመደገፍ በዞናችን የትምህርት ስርጭቱ እንዳይስተጓጎል ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም የገጠር ቀበሌያት ገመድ አልባ ስልክ ዝርጋታ ፕሮግራምን የመደገፍ ስራ ተሰርቷል፡፡

 

 

ማስታወቂያ

ጥበብ ህትመትና ማስታወቂያ

ስለኛ |ካርታ| ያግኙን | ©2005 ጉራጌ ዞን አስተዳደር በጥበብ ህትመትና ማስታወቂያ የተሰራ